Amharic
ለ WA የሚከፈልበት የቤተሰብ እና የህክምና ፈቃድ ማመልከት
በነጻ ለሚቀርቡ የቋንቋ እገዛ አገልግሎቶች በስልክ ቁጥር 833-717-2273 ይደውሉና በመጀመሪያ አማራጭ 7ን ቀጥለው አማራጭ 2ን ይምረጡ። የደንበኛ አያያዝ ሙያተኛው በእንግሊዘኛ መልስ ይሰጥዎታል። ለሙያተኛው የሚናገሩትን ቋንቋ ይንገሩት እና በመስመሩ ላይ አስተርጓሚ እስከሚያገኝ ድረስ ሳይዘጉ እንዲጠብቁ ያደርግዎታል።
በዋሽንግተን ውስጥ ለአብዛኞቹ ሠራተኞች ሁለት ዓይነት የሚከፈልበት ፈቃድ አለ፦
የህክምና ፈቃድ፦ ከባድ የጤና ሁኔታ እንዳይሰሩ ሲከለክልዎት። (የቀዶ ጥገና ሕክምና፣ የአልጋ እረፍት በእርግዝና ወቅት፣ ከወሊድ ወይም ሥር ከሰደደ የጤና ሁኔታ ሕክምና ማገገም።)
የቤተሰብ እረፍት (የጥብቅ ግንኙነት ፈቃድን እና ወታደራዊ የቤተሰብ ፈቃድን ያካትታል)
- ከባድ የጤና እክል ያለበትን የቤተሰብ አባል ለመንከባከብ ጊዜ ለመውሰድ፣
- በቤተሰብዎ ውስጥ ካለው አዲስ ልጅ ጋር በጥብቅ መገናኘት፣ ወይም፦
- የወታደራዊ የቤተሰብ ፈቃድ ወደ ባህር ማዶ ሊሰማራ ካለው ወይም ከተሰማራበት የሚመለስ የቤተሰብ አባል ጋር ጊዜ እንዲያሳልፉ ያስችልዎታል።
ብቁ ለመሆን፣ ባለፈው ዓመት ውስጥ 820 ሰዓታት የሠሩ መሆን አለብዎት። እርስዎ ብዙ ሥራዎችን ቢሠሩም ወይም
አሠሪዎችን ቢቀይሩም እንኳ፣ በዋሽንግተን ውስጥ የተሠሩ ሁሉም ሰዓታት ይቆጠራሉ።
የማመልከቻሂደት
1. ለአሠሪዎ ያሳውቁ
2. ሰነዶችን መሰብሰብ
- የመታወቂያ ማረጋገጫ። ተቀባይነት ያላቸው ሁሉንም ሰነዶች በ paidleave.wa.gov/get-ready-to-apply ላይ ይመልከቱ። ለማመልከት ማህበራዊ የዋስትና ቁጥር አያስፈልግዎትም።
- የጤና ሁኔታ ያለበትን የቤተሰብ አባል ለመንከባከብ ለህክምና ፈቃድ፣ ወይም ለቤተሰብ ፈቃድ፣ ከእነዚህ ውስጥ አንዱን ያቅርቡ፦
- በእርስዎ እና በጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ የተሞላ፤ የከባድ የጤና ሁኔታ ቅጽ ማረጋገጫ።ቅጾችን ያውርዱ።
ወይም፦ - የቤተሰብ ሕክምና ፈቃድ ሕግ ቅጽ
ወይም፦ - እንደ ከባድ የጤና ሁኔታ ማረጋገጫ ቅጽ ተመሳሳይ መረጃን የሚያካትት የዶክተር ማስታወሻ።
- በእርስዎ እና በጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ የተሞላ፤ የከባድ የጤና ሁኔታ ቅጽ ማረጋገጫ።ቅጾችን ያውርዱ።
- ለወታደራዊ የቤተሰብ ፈቃድ፣ ለወታደራዊ ፍላጎት ብዙ ብቁ ምክንያቶች አሉ፣ ስለሆነም ጥያቄዎን ለሚደገፍ ሰነዶች ይለያያሉ። በ FMLA ስር ለወታደራዊ ፍላጎት ምክንያት ፈቃድ እየወሰዱ መሆኑን የሚያሳዩ ሰነዶች ከወታደሩ ወይም ከሌላ ምንጭ ያስፈልጉናል።
- በቤተሰብዎ ውስጥ ከተወለደ ልጅ ጋር በጥብቅ ለመገናኘት ለቤተሰብ ፈቃድ፣ ሁለቱም ወላጆች የልደት የምስክር ወረቀት ቅጽን መጠቀም ይችላሉ። ቅጾችን ያውርዱ።
- በጉዲፈቻ ወይም በቤተሰብዎ ውስጥ ከተቀመጠ ልጅ ጋር በጥብቅ ለመገናኘት ለቤተሰብ ፈቃድ፣ የአሳዳጊ እንክብካቤን፣ የጉዲፈቻ ወይም የአሳዳጊነት ምደባን የሚያሳዩ የፍርድ ቤት ሰነዶችን መጠቀም ይችላሉ። ቅጾችን ያውርዱ።
3. ብቃት ያለው ክስተትዎ እንደ ቀዶ ጥገና፣ ልጅ መውለድ፣ ወይም ከባድ የጤና እክል ያለበትን የቤተሰብ አባል ለመንከባከብ ጊዜ መውሰድ ከተከሰተ በኋላ ለፈቃድ ያመልክቱ።
4. ሳምንታዊ የክሌይም/የይገባኛል ጥያቄዎችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ያውርዱ።
ምንያህልጊዜአገኛለሁ?
- እስከ 12 ሳምንታት የሕክምና ዕረፍት።
- በተመሳሳይ የይገባኛል ጥያቄ ዓመት ውስጥ ከአንድ በላይ ብቃት ያለው ክስተት ካለዎት እስከ 16 ሳምንታት የተቀናጀ የሕክምና እና የቤተሰብ ፈቃድ።
- በእርግዝና ወቅት ከባድ የጤና እክል ካለብዎት እስከ 18 ሳምንታት የተቀናጀ የሕክምና እና የቤተሰብ እረፍት።
የሚከተለው ከሆነ የእርስዎ አሠሪ ሥራዎን ለእርስዎ እንዲጠብቅአይጠበቅበትም፦
- ኩባንያው ከ 50 ያነሱ ሰዎችን ይቀጥራል
- ለኩባንያው ከአንድ ዓመት በታች ሰርተዋል
- ባለፈው ዓመት ለኩባንያው ከ 1,250 ሰዓታት በታች ሠርተዋል